የሰ// 174567

ሚያዝያ 30 ቀን 2012 .

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

     ጳውሎስ ኦርሺሶ

   ፀሐይ መንክር

  መላኩ ካሣዬ

        እስቲበል አንዱዓለም፡፡

አመልካች፡- አቶ ሳሙኤል /ኪዳን

ተጠሪዎች፡- 1/ /ሪት መስከረም አስራት ማሞ

           2/ / ኤልሳቤት ጌታቸው

መዝገቡ ተመርምሮ ከተታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ይህ የሰበር መዝገብ ተከፍቶ ሊቀርብ የቻለው የአሁን ተጠሪዎች በስር ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በአሁን አመልካች ላይ አቅርበው የነበረው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት በማግኝቱ እና በይግባኝ ሰሚ /ቤቱ ስህተቱ ሳይታረም ማለፋ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲሉ አመልካች ሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው መነሻነት ነው፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው /ቤት ተጠሪዎች አቅርበውት የነበረው ክስ በአጭሩ 1981/ በተቋቋመው ሾላ የቤት ሥራ ማህበር ውሰጥ አባል መሆናቸውን እና 1988/ ለማህበሩ ቦታ ተሰጥቶ 1997/ ሽንሻኖ ተሰርቶ ለተጠሪዎች እንደቅደም ተከተላቸው 173 እና 175 . ይዞታ ጐን ለጐን ደርሷቸው ካርታ ተሰርቶ ከተሰጣቸው እና የሊዝ ክፍያም ከፍለው ካጠናቀቁ በኃላ ግንባታ ለመጀመር የውል ግዴታ ገብተው በዝግጅት ላይ እያሉ ተከሣሽ በህገ ወጥ የመሬት ወረራ ፈጽሞና አጥር አጥሮ ሁከቱ የፈጠረባቸው በመሆኑ ሁከት ተወግዶ ይዞታቸውን እንዲያስረክባቸው እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ተይቀዋል፡፡  

ተከሣሽ/ አመልካች በበኩላቸው በሰጡት መልስ የከሣሾችን ይዞታ ያልያዙ እና 750 / ይዞታ ከገበሬ ገዝተው 20 ዓመት ይዘው የከብት በረት የነበረውን ወደ ዶሮ እርባታ ለመለወጥ አስተካክለው እየኖሩበት ያለ መሆኑን በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆንላቸው ጠይቀዋል፡፡

/ቤቱም የየካ ///ማኔጅመንት ይዞታ አስተዳደር አከራካሪ ስለሆነው ይዞታ ማብራሪያ እንዲልክ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ክርክር ያነሳው ይዞታ  የሾላ የቤት ስራ ማህበር መሆኑን እና ካርታም የተሰጣቸው መሆኑን ማብራሪያ ልኮለታል፡፡

/ቤቱም ክርክር ያስነሳው ይዞታ ከላይ የተጠቀሰው ማህበር ሆኖ ለከሳሾች የተሰጣቸው በመሆኑ ተከሣሽም አጥር አጥሮ የያዘ በመሆኑ አጥሩን አፍርሶ ለቅቆ እንዲያስረክብ ሲል ወስኗል፡፡ አመልካች ለፌዴራል ከፍተኛ /ቤት ይግባኝ ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም የይግባኝ ቅሬታው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

ለሰበር አቤቱታ መቅረብ ምክንያት የሆነው ውሳኔ ይህ ሲሆን አመልካች በስር /ቤት ውሳኔ ላይ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲሉ አመልካች መጋቢት 30 ቀን 2011 . በጠበቃቸው አማካይነት የተጻፈ 4 ገጽ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪዎች ክርክር ያስነሳውን ይዞታ በእጅ አድርገው በእውነት አዘውበት የማያውቁ መሆኑ እየታወቀ በሁከት ክስ ሊያቀርቡ የማይችሉ ሆኖ እያለ እኔ ደግሞ ይዞታውን 1990 . ገዝቸ በእጄ ያለ ሆኖ እና አስተዳደሩ ይዞታውን ሽንሻኖ ሊሰራ ለመለካት እንቅፋት ሆነሃል ብሎ የፃፈው ደብዳቤን ለፍ/ቤቱ አቅርቤ ባለበት እንደሁም  20 ዓመት በላይ በግዢ ገዝቼ የምጠቀምበትን ቦታ ለእኔ ካሣ ሳይከፈል እና ምትክ ቦታም ሳይሰጠኝ እንድለቅ መወሰኑ  መሠረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሊታረምልኝ ይገባል በማለት ጠይቀዋል፡፡

የቀረበው አቤቱታ በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ አስተዳደሩ አከራካሪው ይዞታ ያሁን አመልካች ይዟል ከሚል በቀር ከመቼ ጀምሮ እንደያዘ ባልገለፀበት እንዲሁም አመልካች 20 ዓመት በይዞታዬ ሥር መሆኑ ያስረዱኛል በማለት ያቀረቡት የሰው ማረጃ ባልተሰማበት ሁኔታ የሥር /ቤት ሁከት ይወገድ በማለት የወሰነበትን አግባብነት ግራ ቀኙ በተገኘበት ለማጣራት ሲባል ተጠሪዎችን የስቀርባል ሲል ጭብጥ በመያዙ መዝገቡ ለችሎቱ ሊቀርብ ችሏል ፡፡

አቤቱታው ከማስቀረቢያ ነጥብ ጋር ለተጠሪዎች እንዲደርሳቸው ተደርጎ 16/9/2011 .  በጠበቃቸው በአንድነት የተዘጋጀ 4 ገጽ መልስ አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም በአጭሩ፡- አመልካች 20 ዓመት ስለመያዙ ምስክሮች ይሰሙ  ቢባልም ለጉዳዩ አግባብነት አይኖረውም ምክንያቱም አመልካች የይርጋ ክርክር ያላቀረቡ በመሆኑ 20 ዓመት ይዞታውን መያዛቸው ቢመሰከር ውሳኔ አያስለውጠውምና ነው፡፡

ምስክር ቢሰማ እንኳን  የሰነድ ማስረጃዎችን ማስተባበል ስለማይቻል የምስክሮች መሰማት አስፈላጊነት አይኖረውም፣ የክ/ከተማው መሬት ማኔጅመንት /ቤት የላካቸው የሰነድ ማረጃዎች እንዲሁም የአ//ከተማ ካቢኔ ውሳኔ ባለበት በሰው ምስክር ማስተባበል የሚቻል ባለመሆኑ እና ምስክር ብሰማም ባይሰማም ውሳኔውን የማያስለውጠወ በመሆኑ፣ አመልካችም ሆነ ተጠሪዎች 200 አባላት በላይ አባል የሆኑበት ማህበሩ 1988 . ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ይዞታውን  ይዞ የነበረ በመሆኑ የቀዳሚነት የባለይዞታነት መብት ያለው  ማህበሩ በመሆኑ እና እስካሁን 23 ዓመት እድሜ ያላቸው በመሆኑ  ሃያ አመት ይዤዋለሁ ብሎ ምስክር ቢያስማም የሻላ ቤት ሥራ ማህበር መሆኑ ተገቢነት አይኖረውም ፡፡

 አመልካችም እንደማንኛውም አባል 175 . ይዞታ በአባልነቱ ያገኘ ሲሆን እንኳን 20 ዓመት ይዞ ሲያስተዳድር 175 . ይዞታም ሊያገኝ የቻለው 2009 . እንደማንኛውም  የማህበሩ አባል መሆኑን የራሱ ይዞታ ቀደም ብሎ ከተከራከረበት በኃላ ወደ አጎራባች አስፋፍቶ የተጠሪዎችን ቦታ አጥሮ መያዙ በክ/ከተማው መሃንዲሶች የተረጋገጠ በመሆኑ የስር /ቤት ውሳኔ ተገቢ በመሆኑ ሊፀና ይገባል በማለት ሰፊ መልስ አቅርበዋል፡፡ አመልካችም የቀድሞ አቤቱታቸውን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ አቅርበው ከመዝገብ ጋር ተያይዞ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ  በዚህ ተጠናቋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና የመልስ መልስ ከስር /ቤት ውሳኔ እና ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ  አንጻር ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነውም፡- ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው /ቤት የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሲሆን፣ ክርክር  ያስነሳውን ይዞታ በማህበር ተደራጅተን ተሸንሽኖ ለእኛ የደረሰን እና ከአስተዳደሩም ካርታ የወሰድንበትን የአሁን አመልካች በጉልበት ይዞ አጥር ያጠረ በመሆኑ ሁከት ተወግዶ ይዞታችንን ይልቀቅ የሚል ክስ አቅርበዋል፡፡

አመልካች በበኩላቸው ክርክር ያስነሳውን ይዞታ ከከብት እርባታ በረት ጋር 199 . የገዛሁት እና 2 ዓመት በላይ በመያዝ እየኖርኩበት እንዲያውም የከብት ርባታውን ወደ ዶሮ እርባት ለመቀየር ፈቃድ እየጠየኩና በሰነድ አልባም ቦታው በኮሚቴ ተጠንቶ የሚገኘ እንጂ የተጠሪዎች አይደለም፡፡ በሁከት ክስ ለመመስረት አይችሉም፤ ምክንያቱም ክርክር ያስነሳውን ይዞታ ይዘው አያውቁም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር መልስ አቅርበዋል፡፡

በሥር /ቤት አመልካች ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን አስመልከቶ የሥር /ቤት የሰጠው ብይን የሌለ ሲሆን፤ በፍሬ ነገር ክርክሩ ላይ ግን ክርክር ያስነሳው ይዞታ አስተዳደሩን ጠይቄ እንደተረዳሁት ለሻላ ማህበር የተመራ እና ተሸንሽኖም ለአሁን ተጠሪዎች የደረሳቸው መሆኑን ያረጋገጥኩ በመሆኑ አመልካች ሁከት ስለፈጠረ ሁከት ተወግዶ ይልቀቅ ሲል ወስኗል፡፡

አንድ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚያቀርብ  ወገን ንብረቱን በእጅ አድርጎ በእውነት የማያዝበት መሆኑን እና ንብረቱንም የያዘው ባልተጭበረበር መንገድ መሆኑን ማሳየት እንደሚኖርበት  በፍ/// 1149 እና አስቀድሞ ከዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ 36659 እና በሌሎችም መዛግብት በተሰጠው የህግ ትርጉም የማስረዳት ኃላፊነት ይኖርበታል ፡፡

ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ አመልካች ክርክር የተነሳበትን ይዞታ ከከብት ርባታው በፊት ጭምር ገዝቼ እየኖርኩበት 2 ዓመት በላይ የያዝኩት ነው፣ ተጠሪዎች ክርክር ያስነሳው ይዞታ በካርታ ተሰጠን ይበሉ እንጂ ይዘውት የማያውቁ በመሆኑ በሁከት ክስ ሊያቀርብ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡

ተጠሪዎችም ጉዳዩ እዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እስኪደርስ ድረስ ክርክር ያስነሳውን ይዞታ በመሬት ወረራ አመልካች ወረው ይዘውብናል ይላሉ እንጂ ይዞታውን በእጃችን አድርገን እያዘዝንበት ነው በማለት እየተከራከሩ አይደለም፡፡

ሆኖም ግን አመልካች አንስተው የሚከራከሩበት ንብረቱን በእጄ ይዤ እያለ የስር /ቤት አመልካች ያቀረቡት መከራከሪያ የአመልካችንም ምስክሮች መስማት እና በአግባቡ አጣርቶ መወሰን ሲገባው ይህን አልፎ መወሰኑ ከመሰረታዊ የክርክር አመራር ስነ  ስርአት አንጻር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ እና የበላይ /ቤትም የስር /ቤትን ውሳኔ ሳያርም ማለፉ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም፡፡

በመሆኑም አንድ የሁከት ክስ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ሲቀርብ ክሱን ያቀረበው ወገን የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በእጅ አድርጎ በእውነት እየተጠቀመበት ያለ መሆኑን፣ ንብረቱንም  ባልተጭበረበረ  መንገድ የያዘ መሆኑ፣ እንዲሁም ተከሳሽ በዚህ ንብረት ላይ ሁከት የተፈጠረበት መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለበት መሆኑን በመገንዘብ ተጠሪዎች በዚህ ረገድ የሚያቀርቡት ክርክር እና ማስረጃ ካለ በማሰማት እንዲሁም አመልካችም የተጠሪዎችን ክርክር የሚያስተባብሉ መሆኑን በመዘርዘር የሰነድ እና የሰው ማረጃ አቅርቤአለሁ በማለት እየተከራከሩ በመሆኑ የግራ ቀኙን ምስክሮች በማስረጃ ዝርዝር ላይ የቀረቡ ከሆነ ሰምቶ እና የሰነድ ማስረጃንም በአግባቡ በተቀመጠው ስርአት መሠረት ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢ ውሳኔ መስጠት ሲገባው ይህን አልፎ በፍሬ ጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ ሊሻር የሚገባው ነው ብለን ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

  1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ//128057 ጥር 10 ቀን 2011 . በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ እና የፌዴራል ከፍተኛ /ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ//226393 መጋቢት  17 ቀን 2011 . በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/////. 348/1/ መሠረት መሠረታዊ  የህግ ስህተት  የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ  ተሸሯል ፡፡
  2. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በውሣኔ  የዘጋውን መዝገብ እንደገና በማንቀሳቀስ  ከላይ በፍርድ ሃተታው በተገለጸው መሠረት ክርክር ያስነሳው ይዞታን ክሱ በቀረበበት ጊዜ ከግራ ቀኙ ማን ይዞ እንደሚገኝ ከፍ///.1149 አንጻር ሁከት ተፈጠረ በተባለበት የሰነድ ማረጃ እና የሰው ምስክሮች ሰምቶ መርምሮ  በህግ አግባብ ክርክሩን በመምራት ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን በፍ/////. 343/1 መሠረት  መልሰን ልከንለታል፡፡
  3. በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በግራ ቀኙ የወጣ ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል ፡፡
  4. የውሰሳኔው ትክክል ግልባጭ ለስር /ቤቶች ይድረስ ፡፡

መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

/