የመ..196656

                                                                                                            ጥቅምት 01/2016 .

  

 

ዳኞች፡ ተፈሪ ገብሩ(/)

እንዳሻው አዳነ

ተሾመ ሽፈራው

መላኩ ካሳዬ

ነፃነት ተገኝ

 

አመልካች፡-አቶ አሰፋ ሰቦቃ - ቀርበዋል

ተጠሪዎች፡- 1. አቶ አንተነህ ጌታቸው  

         2. የንፋስ ስልክ ላፍቶ /ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር /ቤት       የቀረበ የለም

             3. አቶ ታደሰ ጉራራ

 

መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው፡፡ ሆኖም በጉዳዩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ብይን ሊሰጥበት የሚገባው ጉዳይ በመኖሩ ተከታዩ ብይን ተሰጥቷል፡፡

ብይን

 

የአሁን 2 ተጠሪ ለአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰጠው የፅሁፍ መልስ ውስጥ በዚህ መዝገብ ላይ ክርክር በቀረበበት ጉዳይ ላይ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመቃወም አቤቱታ ቀርቦ በመታየት ላይ ይገኛል የሚል መከራከሪያ አቅርቧል፡፡ እኛም ከፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋናውን መዝገብ በማስቀረብ አጠቃላይ የክርክሩን ይዘት እና አድማስ መርምረናል፡፡

በዚሁ አግባብ የክርክሩ መነሻ የአሁን 1 ተጠሪ በመ//97712 ላይ እንዲሁም አመልካች በመ//107890 በአሁን 2 ተጠሪ እና ሌሎች ግለሰቦች ላይ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የክሳቸው ጭብጥም ሟች / እማዋይሽ ፈንታ የተባሉት ግለሰብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ /ከተማ ወረዳ 11 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የቤት ቁጥር 072 የሆነ ቤታቸውን 1 ተጠሪ 1995 እንዲሁም ለአመልካች 1997 ባደረጉት ኑዛዜ ያስተላለፉ ቢሆንም የአሁን 2 ተጠሪ ቤቱን አልለቅም!” ብሎ ለግለሰቦች እያከራየ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሶ 2 ተጠሪ በፍርድ ኃይል ተገድዶ ቤቱን እንዲያስረክባቸው በየፊናቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን 1 ተጠሪ ክስ ባቀረቡበት ጉዳይ ላይ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ክርክር ተደርጎበት በመ//135182 ላይ ጥቅምት 21/2010 . በተሰጠ ውሳኔ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነጥብ ተመልሷል፡፡ ጉዳዩ በዚህ መልኩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ እያለ የአሁን አመልካች በመ//107890 ላይ ያቀረቡት ክስ ውሳኔ አግኝቶ የክፍለ ከተማው ቤቶች ልማት አስተዳደር /ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታ አቅርቦ በክርክር ላይ የሚገኝ መሆኑ በመታወቁ ፍርድ ቤቱ ሁለቱ መዝገቦች በመ//97712 ተጣምረው እንዲታዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመቀጠልም በሁለቱ መዝገቦች ላይ የቀረበውን ክርክር መርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት በመንግስት የተወረሰ ሳይሆን የወ/ እማዋይሽ ፈንታ መሆኑን፤ ሟችም ይህንን ቤት በኑዛዜ ያስተላለፉት ለአሁን 1 ተጠሪ መሆኑ ጠቅሶ የአሁን 2 ተጠሪ ይህንኑ ቤት 1 ተጠሪ እንዲያስረክብ በማለት ጥቅምት 23/2012 . በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ከዚህ በኋላ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር /ቤት ውሳኔውን በመቃወም አቤቱታውን ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ቀደም ሲል በአሁን አመልካች እና 1 ተጠሪ በተለያዩ መዝገቦች ላይ ቀርበው የነበሩት ክርክሮች ተጣምረው የተስተናገዱ ቢሆንም ሟች / እማዋይሽ ፈንታ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የቤት ቁጥር 072 በኑዛዜም ሆነ ያለኑዛዜ ለማስተላለፍ መብት ያላቸው ስለመሆኑ እንዲጣራ በሚል ከዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በተመለሰው ነጥብ ላይ ተጣርቶ ውሳኔ ያልተሰጠ መሆኑን፤ ይልቁንም ውሳኔው በሟችዋ ያለኑዛዜ እና የኑዛዜ ወራሾች መካከል የቀረበውን ክርክር መሰረት አድርጎ የተሰጠ መሆኑን ማረጋገጡን ተጠቅሶ ከዚህ ችሎት ተለይቶ ከተመለከተው ነጥብ አኳያ ግራ ቀኙ እንዲከራከሩ በሚል ብይን የሰጠ መሆኑን፤ ክርክሩም በዚህ መልኩ በሂደት ላይ እያለ የአሁን አመልካች በዚህ መዝገብ ላይ የሰበር አቤቱታ አቅርበው ጉዳዩም በመታየት ላይ ያለ ስለመሆኑ ለችሎቱ በመገለፁ የዚሁ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ በሚል መዝገቡን ለጊዜው በትዕዛዝ የዘጋ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንግዲህ ከጉዳዩ አመጣጥ እና ከነበረው የክርክር ይዘት በዋናነት ሁለት መሰረታዊ የክርክር መስመሮች መኖራቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡ አንደኛው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው እና ሟች በኑዛዜ አስተላልፈዋል የተባለው ቤት የሟችዋ ነው? ወይስ በመንግስት የተወረሰ ቤት ነው? የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ቤቱ የሟችዋ ነው ቢባል ቤቱን አስመልክቶ ሟች አድርገዋል ከተባሉት ኑዛዜዎች አፈፃፀም አኳያ ከአመልካች እና 1 ተጠሪ መካከል ማን መብት አለው? የሚለው ነው፡፡ የመጀመሪያው ነጥብ አሁን ጭምር በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በክርክር ላይ ያለ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበውን ጉዳይ የሚመለከት ነው፡፡ ሟች አድርገዋል ከተባለው ኑዛዜ አኳያ የቀረበው ክርክር እልባት የሚያገኘው ቤቱ በትክክልም የኑዛዜ አድራጊዋ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ ክስ የቀረበበትን ቤት ባለቤትነት አስምልክቶ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጀመረውን ክርክር ውጤት መጠበቅ ለጉዳዩ አወሳሰን አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በመሆኑም ተከታዩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ 

ትዕዛዝ

 

  1. ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት በመንግስት የተወረሰ አልያም የግለሰብ ቤት መሆኑን  አስምልክቶ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ//97712 ላይ በመካሄድ ላይ ያለው ክርክር ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ክርክር  በፍ/////ቁጥር 197(2) መሰረት ለጊዜው ቆሟል፡፡
  1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ መዝገብ ላይ የተጀመረውን ክርክር ውጤት መጠበቅ ሳያስፈልገው የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮ መወሰን እንዲችል የዚህ ብይን ትክክለኛ ግልባጭ ይድረሰው፡፡
  1. ከፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት የቀረበው ዋናው መዝገብ በተገቢው ጥንቃቄ ይመለስ፡፡
  1. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

/