የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ                            የሰ//ቁጥር 223254

 ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት                                ጥቅምት 05 ቀን 2016 /                                    

                                                         

                                ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

                                        ረታ ቶሎሳ    

  በእወቀት በላይ

                                        ቀነዓ ቂጣታ

ኑረዲን ከድር

አመልካቾች፡-1. አቶ አበባው ታደሰ               ጠበቃ በረከት ቡሽራ ቀረቡ

     2. አቶ ጌታሁን አበባው

ተጠሪዎች፡- 1. / ሃና ወልደገብርኤል ------------------- አልቀረበም

          2. አቶ ቴዎድሮስ ወልደገብርኤል ---------------- ቀረበ

          3. / መኣዛ ወልደገብርኤል ---------------------- አልቀረበም

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ መዝገቡ በዳኞች የእረፍት ጊዜ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

                                    ፍርድ

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 12 ቀን 2014 . ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.. 31835 በቀን 02/03/2014 . የሰጠውን ውሳኔ የኦሮሚያ ጠቅላይ /ቤት በመ.. 382913 በቀን 17/06/2014 . በማጽናት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት እንዲታረምላቸው በመጠየቃቸው ሲሆን ተጠሪዎች በስር /ቤት  ከሳሾች የነበሩ ሲሆን በዚህ ሰበር ክርክር ያልተካተቱ ግለሰብ 1 ተከሳሽ፣ አመልካቾች ደግሞ እንደ ቅደም ተከተላቸው 2 እና 3 ተከሳሽ ሆነው በውል ጉዳይ ተከራክረዋል፡፡

በስር /ቤት ተጠሪዎች በቀን 30/05/2011 . ባቀረቡት ክስ የተጠሪዎች እናትና አባት በህይወት  የሌሉ መሆኑን፣ የአባታቸው ወራሾች መሆናቸውን በአዳማ ወረዳ /ቤት ያረጋገጡ መሆኑን፤ አናትና አባታቸው በህይወት እያሉ በአዳማ ከተማ በድሮው አጠራር ቀበሌ 20 ውስጥ በእናታችው ስም የተመዘገበ 513 . የሆነ የመኖሪያ ቤት ስፋቱ 212 . የሆነ ትርፍ መሬት የነበራቸው መሆኑን እንዲሁም ስፋቱ 539 . የሆነ የቤት ቁጥር 201 የሆነውን በአባታችው ስም የተመዘገበውን ቤት 1991 . ወደ ኤርትራ ሲሸኙ በዚህ የሰበር አቤቱታ ላልተካተተው በስር /ቤት 1 ተከሳሽ ለነበረው ሰው በአደራ ሰጥተውት የሄዱ መሆኑን በመግለጽ ይሁን እንጂ 1 ተከሳሽ በዚሁ ቤት ላይ ካርታ ካወጣ በኋላ በሀሰተኛ ውክልና 1 አመልካች የሸጠው በመሆኑና 1 አመልካችም ስመ ሃብቱን ልጁ ወደ ሆነው ወደ 2 አመልካች በማዞር ካርታውንም አስለውጦ የያዘ በመሆኑ የሽያጭ ውሉ ህገወጥ ነው ተብሎ  359 . ላይ የተሰራው ቤት ፈርሶ አመልካቾች የእናትና የአባታችንን ይዞታ እንዲያስረክቡን ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል፡፡

የስር 1 ተከሳሽም ስፋቱ 359 . የሆነ ይዞታ የሸጥኩ ስለመሆኑ ማስረጃ ስላልቀረበና ሽያጭ የፈጸምኩትም የተጠሪዎች እናት የሆኑት / ወለተ ሀይማኖት አላዘር በሰጡኝ ውክልና በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡

አመልካቾችም በጋራ ሆነው ባቀረቡት መልስ የተጠሪዎች እናት / ወለተ ሀይማኖት አላዘር ለስር 1 ተከሳሽ በሰጡት ውክልና መሰረት ቤቱን 1 አመልካች የሸጠ በመሆኑ በሀሰተኛ ውክልና የተሸጠ በማስመሰል ያቀረቡት ክስ ተገቢነት የለውም፡፡ ውክልናው ሀሰተኛ ስለመሆኑም ሆነ ተጠሪዎች የወ/ ወለተ ሀይማኖት አላዘር ወራሾች ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ የለም፡፡ በሽያጭ ውሉ የተሸጠው ቤት ስፋት 765 . ሲሆን ይህም በተጠሪዎች እናት ስም የካርታ ቁጥር 967/93 በሆነ የተካተተ ሆኖ እያለ ስፋቱ 359 . የሆነ ይዞታ በአባታቸው ስም እንደሚገኝ አስመስለው ማቅረባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ውሉ ጉድለት የለበትም፡፡ ጉድለት አለበት ቢባል እንኳ በቀን 05/03/1993 . በተደረገው ውል የተሸጠው ቤት በጭቃ የተሰራ ግምቱ 60,000.00( ስልሳ ሺህ ብር) የሆነው ፈርሶ ዘመናዊ ቤት ብር 10,000,000.00 (አስር ሚሊዮን) በሚሆን የተገነባበት ስለሆነ ተጠሪዎች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት ያቀረቡት ክስ በመሆኑ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

 ጉዳዩ የቀረበለት የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካቾች የቀረበውን መቃወሚያ ተቀብሎ ውሉ እንዲፈርስ የቀረበው ክስ በይርጋ የታገደ ነው በማለት የተጠሪዎችን ክስ ውድቅ በማድረግ ብይን የሰጠ ቢሆንም ተጠሪዎች በዚህ ብይን ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርበው ፍርድ ቤቱም በተጠሪዎች የቀረበው ክስ የመፋለም ክርክርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን ሽሮ ጉዳዩን ወደ ስር ፍርድ ቤት የመለሰው ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በቀሪ መቃወሚያዎች ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውድቅ አድርጎ በፍሬ ጉዳዩ ላይም የተጠሪዎችን ክስ ተቀብሎ የስር 1 ተከሳሽ ሽያጩን ያከናወነው ቤቱን ለመሸጥ ውክልና ሳይሰጠው ስልጣን ሳይኖረው መሆኑን በመጥቀስ የሽያጭ ውሉን በማፍረስ አመልካቾች አከራካሪውን ቤትና ቦታ ለተጠሪዎች እንዲያስረክቡ ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው  ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠቅላይ /ቤት ውሳኔውን ሽሮ ጭብጦች መስርቶ ጉዳዩ በድጋሚ እንዲታይ በሰጠው መመሪያ መሰረት /ቤቱ ግራ ቀኙን አከራከር ማስረጃዎቻቸውን መርምሮ የተጠሪዎች እናትና አባት በድምሩ አሁን ክስ የቀረበበት 1124 . የጋራ ይዞታ የነበራቸው መሆኑን ከምስክሮች ቃል መረዳት የተቻለ  ሲሆን የተጠሪዎች ወላጆች ድርሻቸውን ያልተከፋፈሉ እንዲሁም የተጠሪዎች አባት ለተጠሪዎች እናት የሰጠው ውክልና የሌለ በመሆኑ እንዲሁም የተጠሪዎች እናት ለስር 1 ተከሳሽ ሰጠች የተባለውን ውክልና በተመለከተም የምስራቅ ሸዋ ዞን በላከው ማስረጃ በፕሮቶኮል ላይ ከመመዝገቡ በቀር የውክልና ሰነዱ በመዝገቡ ያልተገኘ መሆኑን የገለጸ በመሆኑ የተጠሪዎች እናት ለስር 1 ተከሳሽ ውክልና ሰጥታው ቢሆን እንኳ የጋራ ንብረቱን  በግሏ መሸጥ መለወጥ የማትችል በመሆኑ ውክልናው ህጋዊ ውክልና አይደለም፡፡ በመሆኑም ይህን ውክልና መሰረት አድርጎ የተደረገው የሽያጭ ውል ንብረቱን ለመሸጥ ህጋዊ ስልጣን ከሌለው ሰው ጋር የተደረገ ውል በመሆኑ ውሉ ህገ ወጥ ነው፡፡1 አመልካች ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ ባለይዞታዎቹ ሳይቃወሙት የገነባው ቤት አጠቃላይ ግምት ብር 3,604,045.53 (ሶስት ሚልየን ስድስት መቶ አራት ሺህ አርባ አምስት ብር ከአምሳ ሶስት ሳንቲም) መሆኑን በኦሮሚያ የከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ የሚመራ ኮሚቴ ካቀረበው ሪፖርት መረዳት የተቻለ በመሆኑ ተጠሪዎች በፍ///.1179 መሰረት ይህንኑ ግምት ለአመልካቾች ከፍለው ቤቱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ 1 አመልካች ክርክር ያስነሳውን ቤትና ቦታ የገዛበትን ዋጋ እና በክርክሩ ያወጣውን ወጪ ከስር 1 ተከሳሽ የመጠየቅ መብቱ ተጠብቋል በማለት ወስኗል፡፡

አመልካቾችም በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮብናል በማለት ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ /ቤት በተለያየ መዝገብ የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን /ቤቱም ከመረመረ በኋላ የስር /ቤት ውሳኔን በማፅናት ወስኗል፡፡

አመልካቾችም የስር /ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት መጋቢት 12 ቀን 2014 . የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም፦   ከአመልካቾች ጋር የተደረገው የሽያጭ ውል ህዳር 5 ቀን 1993 . የተደረገ በመሆኑና የተጠሪዎች ክስ 2011 . 18 አመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዳል በሚል ያቀረብነውን መቃወሚያ የኦሮሚያ ጠቅላይ /ቤት በመ. 308422 ውድቅ ያደረገው ክሱ የመፋለም ክስ ነው በማለት ሲሆን መጨረሻ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ከሽያጭ ውል ህጋዊነት ጋር ተያይዞ በመሆኑ ይርጋውን ውድቅ ማድረጉ ስህተት ያለበት ነው፡፡  የስር ከፍተኛ /ቤት 1 ተከሳሽ ንብረቱን ያገኘው  በውክልና መሆኑን አረጋግጦ ከተቀበለ በኋላ የተጠሪዎች ክስ እናታችን በሰጠችው ውክልና የአባታችን ድርሻም አብሮ 3 ወገን ተላልፎብናልና የሽያጭ ውሉ ይፍረስልን የሚል ባልሆነበት የተጠሪዎች እናት ውክልና የሰጠችው ስልጣን በሌላት ንብረት ላይ በመሆኑ ውክልናውም ሆነ ሽያጩ ህገወጥ ነው በማለት ከቀረበው ክስ ውጭ መወሰኑ ልናቀርብ የምንችለውን መከላከያ እንዳናቀርብ በማድረግ የመከላከል መብታችንን ያጣበበ አግባብነት የሌለው ነው፡፡

የተጠሪዎች አባት 1984 . ሞተው ተጠሪዎችም የአባታቸው ወራሽነታቸውን በዚሁ አመት ያረጋገጡ ሲሆን ተጠሪዎች ያቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ የአባታቸው ልጆች መሆናቸውን እንጂ ሊወርሱ የሚገባው ንብረት ተጣርቶ የተገለጸበት አይደለም፡፡ የቤቱ ካርታም ለተጠሪዎች እናት የተሰጠው አባታቸው ከሞቱና ወራሽነት ከተረጋገጠ 9 አመት በኋላ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ ወደ አመልካቾች የተላለፈው ህዳር 05 ቀን 1993 . በመሆኑ የተጠሪዎች አባት ከዚህ ቤት ድርሻ እንዳላቸው ለመገመት የሚያስችል መሰረት የሌለ በመሆኑ የተሸጠው ንብረት የባልና የሚስት የጋራ ንብረት ነው ለማለት የሚቻልበት የህግ መሰረት ሳይኖር የስር /ቤቱ የጋራ ነው በሚል መደምደሙ አግባብ አይደለም፤ አመልካች ቤቱ የተጠሪዎች እናት የግል ንብረት መሆኑን የሚያሳዩ የሰነድ ማስረጃዎችን አይቼ በጥንቃቄና በቅን ልቦና የገዛሁ በመሆኑ እንዲሁም ድርሻዬ ተሸጦብኛል የሚለው ወገን ከሻጩ ከሚጠይቅ በቀር ንብረቱ 3 ወገን በሽያጭ ከተላለፈና ስመ ሀብት ከተላለፈ በኋላ የሽያጭ ውሉ ሊፈርስ እንደማይገባ የፌ///ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.. 41857 46527 እና በሌሎችም አስገዳጅ ውሳኔ የሠጠበት ሆኖ እያለ የስር /ቤት ሽያጭ ውሉ ህገወጥ ነው በማለት መወሰኑ ተገቢነት የለውም፤ አሁን እንድለቅ የተወሰነው ቦታ ከሌሎች ሰዎች የገዛሁትን ጨምሮ ይዞታው በሙሉ 1169.25 .  በስሜ ተመዝግቦ እኔም 2 አመልካች በስጦታ ያስተላለፍኩ በመሆኑ እና በቦታው ላይም 20 ክፍል ቤቶች በላይ ተገንብቶ የሚገኝ በመሆኑ የሽያጭ ውሉ በተደረገበት ጊዜ ወደ ነበርንበት ሁኔታ መመለስ አስቸጋሪ ሆኖ እያለ የተገነቡትን ቤቶች ግምት በመቀበል ለተጠሪዎች እንድንለቅ መወሰኑ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 40(3) የሚቃረን ስለመሆኑ የፌ///ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. 1051253010136638 እና ሌሎችም ላይ አስገዳጅ ትርጉም የሠጠበት በመሆኑ፤ ተጠሪዎች ዜግነታቸው ኤርትራዊ በመሆኑ በፍ/ህግ/. 390 በኢትዩጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት መሆን እንደማይችሉ የተደነገገ በመሆኑ እና ግንቦት 07 ቀን 2001 . በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ አንቀጽ 3 የቀድሞ ንብረታቸው ሊመለስላቸው የሚችለው ንብረቱ ያልተሸጠ ከሆነና በወኪሎቻቸው እጅ የሚገኝ ከሆነ ብቻ መሆኑ የተደነገገ ሆኖ እያለ በተያዘው ጉዳይ ንብረቱ 3 ወገን የተላለፈ በመሆኑ የስር /ቤቶች ይዞታው ለተጠሪዎች ይመለስላቸው በማለት የሰጡት ውሳኔ እነዚህን ህጎች የጣሰ ነው፡፡

  በተጠሪዎች አባት ስም የተመዘገበ 359 . በተመለከተ 1956 . የተደረገ የግዥ ውል እንጂ ከአዋጅ ቁጥር47/67 በኋላ በተጠሪዎች አባት ስም የተመዘገበ ይዞታ ስለመኖሩ ምንም አይነት የሰነድ ማስረጃ የሌለ በመሆኑና የቤቶች ግምት በባለሙያ ሳይሆን በወቅቱ የዋጋ ግምት ሊተመን እንደሚገባው የፌ///ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.. 35003 አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቶበት እያለ የስር /ቤት 20 ሚልየን ብር በላይ የሚያወጣውን ቤት በብር 3,604,045.53 (ሶስት ሚልየን ስድስት መቶ አራት ሺህ አርባ አምስት ብር ከአምሳ ሶስት ሳንቲም) ብቻ ገምቶ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተሸሮ በአማራጭ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው፤ ውሉ ፈራሽ ነው የሚባል ከሆኑ አመልካች የወቅቱን የቤቶቹን ግምት ብር 293,410.00 (ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ሺህ  አራት መቶ አስር ብር) ለተጠሪ በመክፈል ቤቱን ማስቀረት ይችላል እንዲባል፣ ተጠሪዎች ግምቱን ለአመልካች ይክፈሉ የሚባል ከሆነ በመሃንዲስ የቀረበው የግንባታ እቃ ግምት ሳይሆን  ቤቱ በአሁኑ ወቅት ሊያወጣ የሚችለው የገበያ ዋጋ ተገምቶ ሊከፈል ይገባል ተብሎ ይወሰንልን የሚል ነው፡፡

አቤቱታው የቀረበለት የሰበር አጣሪ ችሎትም ተጠሪዎች በስር /ቤት ባቀረቡት ክስ አቤቱታ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ኤርትራ ሲሸኙ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት የእህታቸው ባለቤት ለሆነው 1 ተከሳሽ በውክልና ሳይሆን በአደራ ሰጥተው የሄዱ መሆኑን በመጥቀስ የተከራከሩ ሲሆን የስር /ቤት ባደረገው ማጣራት የአመልካች ወላጅ እናት 1 ተጠሪ ቤቱን የሰጡት  በውክልና መሆኑን ባረጋገጠበት ሁኔታ የተጠሪዎች አባት ለተጠሪዎች እናት ውክልና የሰጡ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም 1 ተከሳሽ የተሰጠው ውክልና ህጋዊ አይደለም አመልካቾች ቀድሞ የነበረውን ቤት አፍርሰው ሲሰሩ ተጠሪዎች ስላልተቃወሙ አሁን ያለውን የቤቱን ዋጋ ለአመልካች ከፍለው  ቤቱን እንዲረከቡ በማለት የወሰነበትን አግባብነት ከፍ/////. 246 247 እንዲሁም የፍ///. 1179(2) እና 1180 ለጉዳዩ ያለውን አግባብነት ከመሰረታዊ የክርክር አመራር እና ማስረጃ ምዘና መርህ እና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች ጋር በማገናዘብ መጣራት ያለበት በመሆኑ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ግራ ቀኙም የጽሁፍ ክርክር ይለዋወጡ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በዚህ ትዕዛዝ መሰረት ተጠሪዎች ግንቦት 23 ቀን 2014 . የተጻፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም፦ የተጠሪዎች እናት 1992 . ከዚህ አለም በሞት ተለይተው ባለበት በሽያጭ ውሉ ላይ ለስር 1 ተከሳሽ ውክልና ተሠጠ የተባለው 1996 . ነው፡፡ አመልካች ቤቱን በውክልና ከተሰጠው ከዚሁ ሰው ገዛሁ የሚሉት 1993 . ነው፡፡ በኋላ ላይ 1989 . ተሠጠ የተባለው ውክልናም ቢሆን በባህር መዝገብ ከመመዝገቡ በቀር የሌለ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን 1989 .  በኢትዩያና በኤርትራ መካከል አለመግባባት አልነበረምና የጋራ በሆነው ንብረት ላይ የተጠሪዎች እናት ውክልና ሊሰጡ የሚችሉበት ሁኔታ የሌለ በመሆኑ ውክልናው በሃሰት የቀረበ ነው፡፡ ውክልና አለ ቢባል እንኳ በሽያጭ የተላለፈው ቤት ካርታ ቁጥር 967/93 ካርታ የወጣለት 1993 . በመሆኑ 1989 . ካርታ ቁጥሩ ተጠቅሶ ውክልና ሊሰጥ አይችልም፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎቱ  በያዘው ጭብጥ የስር /ቤት ውክልና 1 ተከሳሽ መሰጠቱ በተረጋገጠበት ይበል እንጂ የስር /ቤቱ ውክልናው ህገ ወጥ ነው በማለት ያልተቀበለው በመሆኑ ይህ ጭብጥ ተገቢነት የለውም፡፡ አመልካቾች ቀድሞ የነበረውን ቤት አፍርሰው ሲገነቡ ተጠሪዎች ስላልተቃወሙ በሚል ከፍ///.1179 አንጻር ለማጣራት በሚል የተያዘው ጭብጥም ቢሆን ቤቱ ሰተላለፍም ሆነ ግንባታው ሲገነባ ተጠሪዎች በአገር ያልነበሩ እና የማያውቁ በመሆኑ ከውጤት እንጻር ይህ ድንጋገጌ የሚቀይረው ነገር አይኖርም፡፡

አመልካቾች የይርጋ መቃዎሚያቸውን እና የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት መሆን አይችሉም የሚለው መቃወሚያቸውን በተመለከተ ብይን ተሰጥቶበት የታለፈ በመሆኑ  ለቀጣይ /ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይገባቸዋል እንጂ በመመሪያ በተመለሰ መዝገብ ላይ በተደረገ ክርክር ሊያነሱ እይችሉም፡፡  በጭብጥ አያያዝ ረገድ ቅሬታ ያለው ወገን ለቀጣይ /ቤት ይግባኝ ማለት ይችላል እንጂ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ /ቤት ጭብጥ ተይዞ በተመራለት መሰረት በሰጠው ውሳኔ ላይ ሊቀርብ አይችልም፡፡ አመልካቾች በጭብጥ ረገድ ያቀረቡት ክርክርም የሌለ በመሆኑ ይህ ክርክር ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የሚገባው አይደለም፡፡ የተጠሪዎች የወራሽነት ማስረጃ በተሸጠው ንብረት ማህደር ውስጥ እስካሁንም ያለ በመሆኑ ንብረቱ የተጠሪዎች እናት ብቻ አለመሆኑን አመልካች እያወቁ የገዙት በመሆኑ የቅን ልቦና ገዥ ሊባሉ አይችሉም፡፡

ከቅን ልቦና ውጭ በህገ ወጥ መንገድ ግንባታ የገነቡ በመሆኑም ከተጠሪዎች የተሻለ መብት አልመሰረቱም፡፡ የውል ህግ አንቀጽ 1817 ተፈጻሚነት የሚኖረው በተዋዋዩች መካካል እንጂ 3 ወገኖች መብት ጎድቶ በተደረገ ውል ላይ አይደለም፡፡ የአዳማ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት /ቤት በተጠሪዎች አባት ስም የተመዘገበ 359 . ስፋት ያለው ቦታ ባልታወቀ አግባብ ወደ አመልካች የዞረ መሆኑን ገልጸው ማህደሩም በችሎት ቀርቦ ውሳኔ የተሰጠበት በመሆኑና አመልካቾችም ክደው ያልተከራከሩ በመሆኑ በዚሀ ችሎት ያቀረቡት ሙግት ተገቢነት የለውም፡፡ በስር /ቤት የተጣራው የንብረቱ ግምት አሁን ያለው የገበያ ዋጋ በመሆኑ በግምት ረገድ የቀረበው ቅሬታ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ የስር /ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ስህተት የለበትም ተብሎ እንዲጸና እንጠይቃለን የሚል ነው፡፡

አመልካቾችም ሰኔ 8 ቀን 2014 . የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ አቤቱታቸውን አጠናክረዋል፡፡     

ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ መሰረት በማድረግ  በውሳኔው ላይ በዚህ ችሎት ደረጃ ሊታረም የሚችል የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡በመሰረቱ የተከራካሪ ወገኖች ክርክር በፍሬ ጉዳይ ላይ ብቻ የተወሰነ ከሆነ ወይም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦ ከሆነ በዚሁ መቃወሚያ ላይ ተገቢው ብይን ከተሰጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ባለጉዳዮቹን የሚያከራክረው የተለያዩበት የህግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ በማረጋገጥ ለጉዳዩ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለውን ጭብጥ በመያዝ  መሆኑን የፍ////.246(1) የሚደነግግ ሲሆን ለሚያዘው ጭብጥ መነሻው በከሳሹ የሚቀርበው ክስ መሆኑ በፍ/////.248() መመልከቱም አንድ ፍርድ ቤት ክርክሩን በአግባቡ ለመምራት መሰረት የሚያደርገውና በመጨረሻም እልባት የሚሰጠው በክሱ የተጠየቀውን ዳኝነት መሰረት በማድረግ መሆኑን ያሳያል፡፡(የፍ/////.182(2) ይመለከቷል፡፡) የተያዙትን ጭብጦች መሰረት በማድረግ የሚሰጠው ውሳኔ የተያዘው ጭብጥ እንዴት እንደተወሰነና የተወሰነበት ምክንያት መገለፅ ያለበት መሆኑን  የፍ////.182(1) የሚያሳይ ሲሆን ስለ እየአንዳንዱ ጭብጥ አወሳሰን የተሰጠው ምክንያት ሁሉ በትችት ላይ መገለፅ ያለበት መሆኑ በቁጥር 182(3) መመልከቱ ፍርድ ቤቱ ለጉዳዩ እልባት ሲሰጥ የግራ ቀኙን ክርክር እንዲሁም ማስረጃ የመዘነበትን ፤የመረመረበትንና ውድቅ ያደረገበትን አግባብ በዝርዝር ማመልከት ያለበት መሆኑን ያሳያል፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ ክሱን ያቀረቡት የቤት ቁጥር 201 እና በዚሁ የቤት ቁጥር ውስጥ የተካተተውን በድምሩ 765 ካሜ ይዞታ በተመለከተ በእናታቸው / ወለተሀይማኖት አላዛር ስም የተመዘገበውን እናታቸው ከአባታቸው ጋር ጋብቻ መስርተው ሲኖሩ ያፈሩትን ቤትና ቦታ እናታቸው ኤርትራዊ በመሆናቸው 14/04/1991 ዓም በመንግስት ተገደው ከሀገር ሲወጡ ለአቶ ገብረማሪያም ብስራት በአደራ የሰጡ ቢሆንም እኚህ የስር 1 ተከሳሽ በሀሰተኛ ውክልና ተጠቅመው 1 አመልካች የሸጠው መሆኑን በአባታቸው ስም ተመዘገበ ያሉትን 359 ካሜ ይዞታ በተመለከተም 1 አመልካች ከወ/ አልማዝ ላቀው ይዞታ ጋር በመቀላቀል 539.45 ካሜ በማድረግ ካርታ በስማቸው አውጥተው 2 አመልካች ማስተላለፋቸውን በመጥቀስ የሽያጭ ውሉ ፈርሶ 359 ካሜ ይዞታ ላይ የተሰራው ቤት ፈርሶ የእናታቸውንና አባታቸውን ይዞታ እንዲረከቡ እንዲወሰንላቸው በመጠየቅ ነው፡፡ተጠሪዎች ከላይ እንደተመለከተው 765 ካሜ ይዞታና ቤትን አስመልክቶ ለስር 1 ተከሳሽ ያስተላለፉት በአደራ መሆኑን ከመግለፅ ውጪ ለስር 1 ተከሳሽ የተሰጠው ውክልና በወ/ ሀይማኖት ድርሻ ላይ ብቻ የተሰጠ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን በማመልከት በአባታቸው ድርሻ ላይ ጭምር የተደረገው የሽያጭ ውል እንዲፈርስላቸው በዚህ አግባብ የሽያጭ ውሉ ሲፈርስም አጠቃላይ በእናታቸው ስም ያለውን ይዞታና ቤት እንዲረከቡ በመጠየቅ ክስ ማቅረባቸውን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡

1 አመልካች አከራካሪውን በተጠሪዎች እናት ስም ተመዝግቦ ይገኝ የነበረውን የተጠሪዎች አባት ይዞታ የሆነውን በማካተት  765 ካሜ ሆኖ በወ/ ወለተሀይማኖት አላዛር ስም ካርታ የተሰራለትን ቤትና ቦታ የወ/ ወለተሀይማኖት  ወኪል ከሆነው የስር 1 ተከሳሽ ጋር  05/03/1993 ዓም በተደረገ የግዢ እና ሽያጭ ውል በህጉ አግባብ ገዝተው ግምቱ ብር 10,000,000.00 የሚያወጣ ግንባታ ያከናወኑበትና አሁንም ድረስ ይዘውት የሚገኙት መሆኑን ጠቅሰው የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪዎች ይህ ውክልና በሀሰት የተዘጋጀ መሆኑን፤እናታቸው ለስር 1 ተከሳሽ የሰጡት ውክልና አለመኖሩን ይዞታውና ቤቱ በስር 1 ተከሳሽ እጅ የገባው በአደራ እንዲጠብቁት መሆኑን ገልፀው የተከራከሩ ቢሆንም 2 እና 3 የተጠሪዎች ምስክሮች እናታቸው ለስር 1 ተከሳሽ የሰጡት ውክልና መኖር አለመኖሩን የማያውቁ መሆኑን ሲያስረዱ 1 የተጠሪዎች ምስክር ብቻ (ለተጠሪዎች ምስክር ሆነው የቀረቡት ተጠሪዎች መሆናቸውን ልብ ይሏል) እናታቸው ለስር 1 ተከሳሽ የሰጡት ውክልና የሌለ መሆኑን በመጥቀስ ያስረዱ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት ለምስራቅ ሸዋ ዞን ዐቃቤ ህግ /ቤት ተገቢውን ትዕዛዝ ሰጥቶ ባደረገው ማጣራት በፕሮቶኮል መዝገቡ ላይ / ወለተሀይማኖት አላዛር  ለውክልና ተቀባይ አቶ ገብረማሪያም ብስራት (የስር 1 ተከሳሽ) ውክልና መስጠታቸውን የሚያሳይ ተመዝግቦ መገኘቱን መጥቀሱ ከተጠሪዎች ክስና ክርክር  ይልቅ የአመልካቾች ክርክር በአስተዳደር መስሪያ ቤቱ ምላሽ የተደገፈ መሆኑን ያሳያል፡፡

ማስረጃን የመስማት፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶች በዋነኝነትም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  የተጠሪዎች እናት ለአቶ ገብረማሪያ ብስራት ተገቢውን ውክልና መስጠታቸውን ከዚህ ላይ ለመረዳት የሚቻለው የከሳሾች እናት 1 ተከሳሽ ውክልና የሰጠች ሲሆን …” የሚል ሀረግ በውሳኔው ላይ በማካተት አረጋግጦ የሽያጭ ውሉ ፈርሶ አከራካሪውን ቤትና ቦታ አመልካቾች ለተጠሪዎች እንዲያስረክቡ የወሰነው እንደ ተጠሪዎች ክስ አቀራረብ ውክልናው በሀሰት የተዘጋጀ መሆኑን በማረጋገጥ ሳይሆን ከተጠሪዎች ክስና የዳኝነት ጥያቄ ውጪ የሽያጭ ውሉ ውክልና ከተሰጠበት ድርሻ በማለፍ በተጠሪዎች አባት ድርሻ ላይ ጭምር መደረጉን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ይህም የስር ፍርድ ቤቶችየፍ/////.182(2)246(1) እና 248() ድንጋጌ ውጪ ከተጠየቀው ዳኝነት ውጪ፤ከግራ ቀኙ ክርክር ውጪ ጭብጥ በመያዝ ለግራ ቀኙ ክርክር እልባት መስጠቱን ያሳያል፡፡

 የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች ለክሳቸው መሰረት ካደረጉት የዳኝነት ጥያቄ ውጪ በመውጣት ፍርድ ማሳረፋቸው እንደተጠበቀ ሆኖ አከራካሪው ቤትና ቦታ 1 አመልካች የተላለፈው በወ/ ወለተሀይማኖት ስም ካርታ ተዘጋጅቶለት መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ከመረጋገጡ አንፃር በሰበር መዝገብ ቁጥር 4185746527 እና በተመሳሳይ መዝገቦች  የውርስ ንብረት በሆነ ቤትና ቦታ ላይ ድርሻ አለን የሚሉ ወገኖች ንብረቱን ህጋዊ የሆነ የባለቤትነት ማረጋጫ ይዞ ከነበረ ሰው በመግዛት ስመ ሀብቱን ወደራሱ አዛውሮ የሚገኝን ሰው ለመጠየቅ የማይችሉ መሆኑን በማመልከት የሠጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ከግምት ውስጥ ያላስገባበትን የህግ አግባብ በውሳኔው ላይ አላመለከተም፡፡

1 አመልካች አከራካሪውን ቤትና ቦታ በሽያጭ ውል በእጃቸው ያስገቡት / ወለተሀይማኖት ብስራት ለስር 1 ተከሳሽ በሰጡት ውክልና መሰረት በወ/ ወለተሀይማኖት ብስራት ስም በይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መመዝገቡን መሰረት አድርገው መሆኑ ከላይ በተመለከቱት አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች አግባብ ተጠሪዎች ቤቱንና ይዞታውን አስመልክቶ 1 አመልካች ላይ ክሱን ከማቅረብ የሚያግዳቸው መሆኑን፤ ከዚህ ይልቅ ከሽያጩ ገንዘብ ላይ ድርሻቸውን የመጠየቅ መብትን የሚሰጣቸው መሆኑን ከላይ የተመለከቱት አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች የሚያመለክቱ ሆነው እያለ የስር ፍርድ ቤቶች 1 አመልካች ላይ የቀረበውን ክስ ተቀብሎ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስና አመልካቾች አከራካሪውን ቤትና ቦታ ለተጠሪዎች እንዲያስረክቡ መወሰናቸው ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ያሳያል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪዎች በአባታቸው ስም የሚታወቅ ቀሪ ይዞታ መኖሩን ጠቅሰው ክሱን ሲያቀርቡ አመልካቾች የአባታቸው ይዞታ ተጠቃልሎ በወ/ ወለተሀይማኖት ብስራት ስም ካርታ የተሰራበት መሆኑን፤መኖሪያ ቤት የሰሩበትን ቦታ አቶ አወል ከተባለ ሰው በገዙትና ቀሪውን የስር 1 ተከሳሽ በውክልና በሸጠው ከፊል ይዞታ ላይ የሰሩት መሆኑን ገልፀው ከመከራከራቸው አንፃር  በፍትሐ ብሄር ክርክር አንድ መብት አለ ብሎ የሚከራከር ወገን መብቱ መኖሩን የማስረዳት ሸክም ያለበት መሆኑን ይህ መብት መኖሩን ካላስረዳ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ ሊያደርገው የሚገባ መሆኑን፤ አንድ ንብረት ይገባኛል በማለት የሚከራከር ወገን ንብረቱ መኖሩን የርሱም መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ካላቀረበ ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ የሚገባ መሆኑን በማመልከት በሰበር መዝገብ ቁጥር 44364  እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው መዝገቦች  አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶ እያለ 1 ተጠሪ በአባታችን ስም የተመዘገበው ይዞታ ጀርባ የእናታችን መሬት ያለው አንድ ቦታ ውስጥ ነው፡፡ በማለት የእናትና አባታቸው ይዞታ በአንደነት የሚገኙ መሆኑን በማመልከት በአመልካቾች ክርክር አግባብ አስረድተው እያለ ከዚህ በተለየ መልኩ ሁለቱ ይዞታዎች መለያ ተደርጎላቸው የሚገኙ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ ማረጋገጫ ባልቀረበበት የሽያጭ ውሉ ውክልና ባልተሰጠበትም ንብረት ላይ የተደረገ ነው በማለት መደምደሙ ከማስረጃ ምዘና መሰረታዊ መርህ አንፃር መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀማቸውን ያሳያል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የስር ፍርድ ቤት ውሉ ሊፈርስ ይገባል የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ የግራ ቀኙን ክርክር ከውል ህግ መሰረታዊ መርሆች አንፃር በመመርመር ለጉዳዩ ተገቢውን እልባት መስጠቱን እያሳያ ይህ ከሆነ ደግሞ ከውል ህግ መሰረታዊ ድንጋጌዎች የፍ///.1815 እና 1817 አንፃር ግራ ቀኙ ከውሉ መፈፀም በፊት ወደነበሩበት ሊመለሱ ይችላሉ ወይስ አይችሉም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ለግራ ቀኙ ክርክር እልባት ሊሰጥ ሲገባ ለጉዳዩ አግባብነት የሌለውን ድንጋጌ የፍ///.1179 በመጥቀስ፤በይዞታው ላይ ተገንብተው የነበሩት ግምታቸው ብር 293,410.00 የነበረው ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ፈርሰው በድምሩ ዋጋቸው ብር 3,604,045.53 የሚያወጡ ቤቶች በአመልካቾች መገንባታቸውን የምስክሮቹ ቃልና የሰነድ ማስረጃዎቹ እያሳዩ ይህም ግራ ቀኙን ወደነበሩበት መመለስ በፍ///.1817(1) መሰረት ከፍ ያለ መሰናክልን የሚያስከትል መሆኑን እያሳየ፤ተጠሪዎች ይዞታውንና ቤቱን እንዲረከቡ ማድረግ የሚቻለው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ከሀገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩ ኤርትራዊያን በኢትዮጲያ ውስጥ ያላቸውን ንብረት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው መመሪያ አንቀፅ 3 መሰረት ንብረቶቹ ካልተሸጡ ወይም ካልፈረሱ ብቻ ሆኖ እያለ አሁን በያዝነው ጉዳይ ግን የተጠሪዎች ወላጆች በይዞታው ላይ ያከናወኑት ግንባታ 1 አመልካች በሽያጭ ተላልፎ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ፈርሶ በአመልካቾች ግንባታ የተተካ መሆኑ ማስረጃን የመስማት የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጦ እያለ  የተጠሪዎች የዳኝነት ጥያቄ በይዞታው ላይ አመልካቾች ያከናወኑት ግንባታ ፈርሶ ቤቱን ለመረከብ የሚጠይቅ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ከዚህ በማለፍ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቤቶቹን የግንባታ ዋጋ ተጠሪዎች ለአመልካቾች ከፍለው፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ደግሞ የቤቱን የገበያ ዋጋ ተጠሪዎች ለአመልካቾች በመክፈል ይዞታውንና ቤቱን እንዲረከቡ መወሰናቸው ከላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችና በሰ//.3933647617 እና በተመሳሳይ መዝገቦች የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ወስነናል፡፡ 

                                    ውሳኔ

1. የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.. 31835 በቀን 02/03/2014 . የሰጠው ውሳኔና ይህንን ውሳኔ በማፅናት የኦሮሚያ ጠቅላይ /ቤት በመ.. 382913 በቀን 17/06/2014 . የሰጠው ውሳኔ    በፍ////.348(1) መሰረት ተሸሯል፡፡

2. በአዳማ ከተማ ከፍተኛ 2 ቀበሌ 20 ውስጥ የሚገኘውን አከራካሪውን ቤትና ቦታ 1 አመልካች የተጠሪዎች ወላጅ እናት ለአቶ /ማሪያም ብስራት በሰጡት ውክልና መነሻነት በሽያጭ ውል ያገኙት በመሆኑ የሽያጭ ውሉ ፈርሶ አመልካቾች ለተጠሪዎች የሚያስረክቡበት የህግ አግባብ የለም ብለናል፡፡

3. ይህ ውሳኔ ተጠሪዎች የሽያጩን ገንዘብ ቤቱንና ቦታውን በሽያጭ ባስተላለፉት አቶ /ማሪያም ብስራት ላይ ክስ አቅርበው ከመጠየቅ የሚያግዳቸው አይደለም ብለናል፡፡

4.ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

/