የሰ.. 225482

                                                              ቀን ጥቅምት 6/ 2016.

                            ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

                                  ደጀኔ አያንሳ

                                  ብርቅነሽ እሱባለው

                                  ሀብታሙ እርቅይሁን

                                  ብርሃኑ መንግስቱ

አመልካች፡ / አለሚቱ አድማሴ - አልቀረቡም

ተጠሪ፤ አቶ ካሳ ስጦቴ - ወኪል - መሰረት ካሳ - ቀረቡ 

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

                            ፍርድ

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ የቀረበው አመልካች የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. 03-3429 28/7/14. በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት 9/8/14. በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት በተጠሪ እና አሁን የሰበር ክርክሩ ላይ በሌለው የደሴ ከተማ አስተዳደር////ከተማ(ስር 2 ተጠሪ) ላይ ባቀረቡት የፍርድ መቃወም አቤቱታ ተጠሪ (ስር 1 የመ/ተጠሪ) አሁን የሰበር ክርክሩ ላይ የሌለውን ስር 2 ተጠሪን ካርታ ሊሰራልኝ ይገባል በማለት ያቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን /ቤቱ ስልጣን የለውም፡፡ ክሱን በይርጋ ይታገዳል፡፡ እንዲሁም 1993. ተጠሪ በስጦታ ለአመልካች የሰጠኝ 467.88. ሆኖ እያለ /ቤቱ 467.88. ላይ 75. ተቀንሶ በተቀረው ላይ ለተጠሪ(ስር 1 ተጠሪ) ካርታ ሊሰራ ይገባል በማለት መወሰኑ አግባብነት የለውም፡፡ ስለሆነም ፍርድቤቱ 26/8/12. የሰጠው ፍርድ በፍ///// 360(2) መሰረት ይሻርልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ማስረጃዎችንም አቅርበዋል፡፡

ተጠሪ(ስር 1 ተጠሪ) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን አቅርበው በፍሬጉዳዩ ላይ ባቀረቡት መልስ ካለኝ አጠቃላይ ይዞታ ውስጥ 75. ለአመልካች የሰጠሁ በመሆኑ ይህ ተቀንሶ በተቀረው ላይ ካርታ ሊሰራለት የሚገባ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡ ስር 2 ተጠሪም ባቀረበው መቃወሚያ እና መልስ ከክርክሩ ውጪ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

ፍርድቤቱም ክሱን ሰምቶ የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች በብይን ውድቅ አድርጎ፤ ፍሬጉዳዩን በተመለከተ ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን ከፍ///// 358 አንጻር መርምሮ አመልካች በማስረጃነት ያያዘችው ከተጠሪ ጋር 14/10/93. የተደረገው ስጦታ ውል የቤ. 176() የሚመለከተው 467.88. ይዞታን ነው ወይስ ተጠሪ እንደሚከራከሩት 75. ነው የሚለው ነጥብ በተመለከተ /ቤቱ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዲረዳው የአመልካች እና ተጠሪን ማህደር አስቀርቦ እንደመረመረው የሁለቱም ሰዎች ማህደር ላይ 14/10/93. የስጦታ ውል ካደረጉ በኋላ ወደሚመለከተው የመንግስት ተቋም በመሄድ የቤት ቁጥር 176() ላይ የስመንብረት ዝውውር እንዲደረግ የጠየቁ እና የቤ. 176() የሆነው ቤት በአመልካች ተላልፎ የተመዘገበ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህን የንብረት ማስተላለፊያ ፎርም አመልካች እና ተጠሪ ሲሞሉ የቤ. 176() የሆነው ቤት ያረፈበት ይዞታ 75. መሆኑን አስፍረው የንብረት ዝውውሩም በዚህ አግባብ ተፈጽሞ የማህደራቸው አካል ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ለአመልካች የሰጣት ቤት ቁጥር 176() ያረፈበት ይዞታ 75. መሆኑ ከተረጋገጠ ተጠሪ ካለው አጠቃላይ 467.88. ላይ ለአመልካች የሰጣት 75. ተቀንሶ በተቀረው ይዞታ ላይ ለተጠሪ ካርታ የማይሰራበት አግባብ ባለመኖሩ በማለት /ቤቱ 26/8/12. ተጠሪ ከነበራቸው ህጋዊ ይዞታ 467.88. ውስጥ ለአመልካች በደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ውልና ማስረጃ 1993. በስጦታ 75. ላይ ያረፈውን የቤ. 176() የሆነውን ቤትና ቦታ በመቀነስ ለተጠሪ ቀሪ ይዞታ ካርታ ሰርቶ እና አስተካክሎ እንዲሰጥ በማለት የሰጠውን ውሳኔ በማጽደቅ ወስኗል፡፡

አመልካች ከላይ በተገለጸው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ /ቤት አቅርበው /ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡ በዚሁ ላይ በአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ /ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተጠሪን መልስ ከተቀበለ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ ተጠሪ ከአከራካሪው 467.88. ይዞታዬ ላይ ለአመልካች ስጦታ ካደረኩበት የቤ. 167() ውጪ ሌሎች የቤ. 167() እና የቤ. 167() ቤቶች ያረፉበት ነው ሲሉ ላቀረቡት ክርክር አመልካች ማስተባበያ ያላቀረቡ መሆኑ፤ 14/10/93. በተጻፈ ተጠሪ ለአመልካች ያደረገው የስጦታ ውል 467.88. ቦታ ውስጥ ካርታና ፕላኑ የድሮ ቤት ስለሆነ የሌላው የቤ. 167() የሆነውን ስጦታ ያደረገበት መሆኑ የሚነበብ መሆኑ፤ የቦታው መጠን በስጦታ ውሉ ላይ 75. ብቻ መሆኑ የተለየ ባይሆንም ተጠቃሎ ሲታይ 467.88. ቦታ ላይ ያረፈውን የቤ. 167() ከአጠቃላይ ይዞታ ቦታው ጋር ስጦታ አድርጓል የሚል ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ስለሆነም ክሱ በቀረበበት 2012. ስራ የነበረው መመሪያ ዝቅተኛው የቦታ ሽንሻኖም ሆነ ምሪት 100. ሆኖ እያለ የስጦታ ውሉ የቦታውን መጠን ያልለየና ለትርጉም የተጋለጠ ሆኖ እያለ ተጠሪ ለአመልካች ስጦታ ያደረገላት 75. ተቀንሶ በቀረው ቦታ ለተጠሪ ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ሊታረም የሚገባው ነው በማለት የስር /ቤቶችን ውሳኔ እና ትእዛዝ በማሻሻል ተጠሪ ለአመልካች ስጦታ ያደረገው የቤ. 167() ያረፈበትን ቦታ በከተማው በነበረው የመኖሪያ ቦታ የሽንሻኖ ስታንዳርድ መሰረት 100. ተቀናንሶ ለተጠሪ በቀረው ይዞታ ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች ከላይ በተገለጹት ውሳኔ እና ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ለዚህ የሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የአብክመ ጠቅላይ /ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ባልተጠየቀ ዳኝነት ላይ በመመስረት የደሴ ከተማ ነክ /ቤቶች ከመነሻ በዚህ ጉዳይ ላይ ግራቀኙን አከራክሮ ለመወሰን የሚያስችል ስልጣን ነበራቸው አልነበራቸውም? የአዋጅ ቁጥር 245/09 አንቀጽ 79 ስር የተቀመጡትስ ድንጋጌዎች ለፍ/ቤቱ ይህን ስልጣን የሚሰጡ ናቸው ወይ? በሚለው መሰረታዊ ነጥብ ላይ ምንም ሳይል በዝምታ ማለፉ፤ የስር /ቤቶች ይህን ጉዳይ ተቀብሎ ለማከራከር ሆነ ለመወሰን የሚያስችል ስልጣን አላቸው ከተባለስ በተለይ የመጀመሪያ ደረጃ /ቤቱ ለክርክር መነሻ የሆነውን የውል ሰነድ መሰረት በማድረግ ግራቀኙን በችሎት ሳያከራክር፤ ለክርክሩ አግባብነት ያለውን ጭብጥ ሳይመሰርት፤ በግራቀኙ የተቆጠሩትን የሰው ምስክሮች አስቀርቦ ሳይሰማ ይህን ውሳኔ መስጠቱ ስነስርአታዊ ነበር ወይ የሚለውን ሁሉ በአግባቡ ሳይመረምር በቀጥታ በፍሬጉዳዩ ላይ በማተኮር በከተማው ስታንዳርድ መሰረት ለአመልካች 100. ተቀንሶ በቀሪ ይዞታ ላይ ለተጠሪው ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በሚል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲሻር በማለት ጠይቀዋል፡፡

ይህ አቤቱታቸው በሰበር አጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ በሰበር አመልካች ለክልሉ የቀረበው የሰበር አቤቱታ እና 14/10/93. የተጻፈ ውል መሰረት ያደረገ ነው አይደለም? የሚለውን ለማጣራት ለሰበር ችሎቱ ይቅረብ ተብሎ 22/9/14. በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ 6/10/14. በተጻፈ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ሊደረግ ይገባል የሚሉበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡ ተጠሪ በበኩላቸው ለዚህ የሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረቡት መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ የክልሉ ጠቅላይ /ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት 2012. የነበረው መመሪያ ዝቅተኛ የመሬት ሽንሻኖ የቦታ መጠን 100. እንደነበር በውሳኔው ላይ ቢገልጽም የትኛው መመሪያ? የትኛው አንቀጽ? የሚለውን የማይለይ እና የማያስቀምጥ በመሆኑ መመሪያው በእውነትም አለን? ካለስ ተሻሽሏል ወይስ ተሽሯል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ የማይችል ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠሪ ለአመልካች ቤቴን ከነአረፈበት ቦታ መጠን ብቻ ሰጠሁኝ እንጂ አመልካች ቦታውን በሽንሻኖ አላገኘችውም፤ የሽንሻኖ ቦታ ማለት ግለሰቦች ከመንግስት ለቤት መስሪያ የሚያገኙት ቦታ እንጂ ግለሰቦች ለግለሰቦች በስጦታ የሚያስተላለፉት ቦታ እንዳልሆነ እየታወቀ አግባብነት ከሌለው እና ከሽንሻኖ ጋር በማገናኘት ውሳኔ መስጠቱ ስህተት ነው፡፡

ተጠሪ(በመስቀለኛ የሰበር አቤቱታ አመልካች) 467.88. ውስጥ የሚገኘውን 176() ቤቴን ለአመልካች የሰጠሁኝ መሆኔ በአጠቃላይ ባለኝ 467.88. ውስጥ 176() 176() እና 176() የሚባሉ ቤቶች ያሉኝ መሆኑ፤ የስጦታ ውሉ ከተደረገ በኋላ የስመንብረት ዝውውር ሲደረግ 75. ላይ ያረፈው 176() ቤት በአመልካች ስም መመዝገቡ እና በዚሁ የቦታ መጠን ግብር ስትገብር የነበረ መሆኑ መረጃ የመመዘን እና የማጣራት ስልጣን ያላቸው ፍርድቤቶች ከማረጋገጣቸውም በተጨማሪ የክልሉ ጠቅላይ /ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ይህን አረጋግጧል፡፡ እነዚህ ፍሬነገሮች አልተሟሉም አላለም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ከፈቀድኩትና ከተስማማሁበት ውጭ 25. ቦታ እንድጨምር ተደርጎ ውሳኔ መስጠቱ፤ የክልሉ ጠቅላይ /ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ሆነ የከተማ ነክ /ቤቶች እንዳረጋገጡት የደሴ ከተማ ከንቲባ /ቤት ለተጠሪ 75. ቦታ ከነቤቱ ተቀንሶ ለተጠሪ(መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ አመልካች) ካርታ እንዲሰራልኝ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ውሳኔው በየትኛውም የመንግስት ተቋም አልተሻረም፤ ከንቲባ /ቤትም ውሳኔውን ሲሰጥ ለአመልካች የተሰጣት የቦታ መጠን ራሱን ችሎ መለየት እና ካርታ ሊሰራለት እንደሚችል በመግለጽ እና በግዜው ያለውን መመሪያ ለማስፈጸም ችግር እንደማይፈጥር በመግለጽ ሲሆን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የማይታወቅ 2012. ዝቅተኛ የቦታ ሽንሻኖ መጠን 100. ስለሆነ በዚሁ ልክ ቦታ እንዲሰጥ በማለት የሰጠው ውሳኔ ስህተት በመሆኑ ተሽሮ የከተማ ነክ /ቤቶች ውሳኔ እንዲጸና፤ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡

በተጠሪ የቀረበው መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ለአመልካች 14/10/93. በተደረገ የስጦታ ውል የቤ. 176() በሆነው ቤት ላይ ስጦታ ያደረጉበት ቦታ መጠኑ 75. መሆኑ በስር /ቤቶች በፍሬነገር ደረጃ በተረጋገጠበት ሁኔታ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ክስ በቀረበበት 2012. በነበረው መመሪያ ዝቅተኛው የቦታ ሽንሻኖም ሆነ ምሪት 100. በመሆኑ ተጠሪ ለአመልካች ስጦታ ያደረገላት 75. ተቀንሶ በቀረው ቦታ ለተጠሪ ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በማለት የስር /ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ እና ትእዛዝ በማሻሻል ተጠሪ ለአመልካች ስጦታ ያደረገው የቤ. 176() ያረፈበትን ቦታ በከተማው በነበረው የመኖሪያ ቦታ የሽንሻኖ ስታንዳርድ መሰረት 100. ተቀናንሶ ለተጠሪው በቀረው ይዞታ ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት የተጠሪ መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ችሎቱ ይቅረብ ተብሎ 26/5/15. በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ 15/6/15. በተጻፈ ባቀረቡት መልስ የስር /ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚሉበትን ምክንያት በመዘርዘር እንዲሻር ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ 30/6/15. በተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

ይህ የሰበር ሰሚ ችሎትም በአመልካችም ሆነ በተጠሪ የቀረበውን የሰበር እና መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢዎቹ የህግ ድንጋጌዎች አንጻር የስር /ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን እንደሚከተለው መርምሯል፡፡

የተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 281/2014 አንቀጽ 24(1) የክልል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት(መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት በዚህ አንቀጽ 2(4)(-) እንደተዘረዘረው) ተፈጽሞበታል በሚል የሚቀርቡለትን እና ከአንቀጽ - የተመለከቱትን ጉዳዮች በሰበር የማየት እና የመወሰን የዳኝነት ስልጣን አለው በማለት ደንግጓል፡፡    የካርታ ይሰራልኝ የዳኝነት ጥያቄን ተቀበሎ የማየት የስረነገር ስልጣን ያለው የመጀመሪያ ደረጃ የከተማ ነክ ጉዳዮች /ቤት ስለመሆኑ ከተሻሻለው የአማራ ክልል ከተሞች እንደገና ማቋቋሚያ፤ ማደረጃና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 245/2009. አንቀጽ 79(1) ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ነው፡፡

አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የስር የደሴ ከተማ ነክ /ቤቶች ከመነሻውም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ ላይ ግራቀኙን አከራክሮ ለመወሰን የሚያስችል ስልጣን አልነበራቸውም ሲሉ ያቀረቡትን ክርክር በተመለከተ ተጠሪ መጀመሪያ በስር /ቤት በደሴ ከተማ አስተዳደር ሰኞ ገበያ /ከተማ ላይ አቅርበውት የነበረው ክስ ከነበረኝ 467.88. ውስጥ ለአመልካች በስጦታ የሰጠሁት የቤ. 176() የሆነውን ቤትና ቦታ ተቀንሶ የተጠሪን ቀሪ ይዞታ ካርታ ሰርቶና አስተካክሎ እንዲሰጠኝ የሚል በመሆኑ ከላይ በተገለጸው አዋጅ ቁጥር 245/2009 አንቀጽ 79(1) ድንጋጌ መሰረት የደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን ያለው በመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር ይህ የሰበር ሰሚ ችሎት አልተቀበለውም፡፡

በያዝነው ጉዳይ ፍሬጉዳዩን በተመለከተ ማስረጃዎችን የመስማት፤ የመመርመር እና የመመዘን በህግ ስልጣን የተሰጠው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት በአመልካች በፍ///// 358 መሰረት የቀረበለትን የፍርድ መቃወም አቤቱታ መነሻ በማድረግ ክርክሩን መርቶ ተጠሪ 14/10/93. በተደረገ የስጦታ ውል 467.88. አጠቃላይ ይዞታው ውስጥ ለአመልካች የሰጣት የቤት ቁጥር 176() ያረፈበት ይዞታ 75. መሆኑን በማስረጃ በፍሬነገር ደረጃ አረጋግጦ ሳለ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ /ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በስር /ቤቱ ከተረጋገጠው እና ከተደረሰበት ድምዳሜ ውጪ በመሄድ እንዲሁም በክልሉ ፍርድቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ማስረጃን በመመርመር ክሱ በቀረበበት 2012. ስራ የነበረው መመሪያ ዝቅተኛው የቦታ ሽንሻኖም ሆነ ምሪት 100. ሆኖ እያለ የስጦታ ውሉ የቦታውን መጠን ያልለየና ለትርጉም የተጋለጠ ሆኖ እያለ ተጠሪ ለአመልካች ስጦታ ያደረገላት 75. ተቀንሶ በቀረው ቦታ ለተጠሪ ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ሊታረም የሚገባው ነው በማለት የስር /ቤቶችን ውሳኔ እና ትእዛዝ በማሻሻል ተጠሪ ለአመልካች ስጦታ ያደረገው የቤ. 167() ያረፈበትን ቦታ በከተማው በነበረው የመኖሪያ ቦታ የሽንሻኖ ስታንዳርድ መሰረት 100. ተቀናንሶ ለተጠሪ በቀረው ይዞታ ካርታ ተሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በማለት የሰጠውን ውሳኔ ይህ የሰበር ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝቶታል፡፡ ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል፡፡

                               ውሳኔ

  1. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. 03-3429 28/7/14. የሰጠው ውሳኔ በፍ///// 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡
  2. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ. 540/12 6/11/13. የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት የደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ /ቤት በመ. 1528/2013 27/11/13. የሰጠው ትእዛዝ በፍ///// 348(1) መሰረት ጸንተዋል፡፡
  3. በዚህ የሰበር ሰሚ ችሎት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ አመልካች እና ተጠሪ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡
  4. የውሳኔው ግልባጭ ለስር /ቤቶች ይድረስ፡፡
  5. መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ  የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

/